Herd Immunity ምንድነው? - a podcast by Yetenaweg@gmail.com
from 2020-04-02T18:07:10
በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ Herd Immunity ከበሽታ ሊጠብቀን አይችልም። መኖሩንም ማወቅ አንችልም። የተነገሩንን የመከላከል እርምጃዎች እንከተል። Tweet
Herd Immunity ማለት በአንድ ማህበረሰብ ያሉ ሰዎች ውስጥ ለ አንድ ተላላፊ በሽታ ምን ያህሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ነው የሚነግረን። ሰዎች ይሄን የመከላከል አቅም ወይ ታመው ከበሽታው ሲያገግሙ ያገኙታል ወይም በ ሕብረተሰብ ጤና የሚመረጠው ደግም ማህበረሰብ አቀፍ በሆነ የክትባት ዘመቻ ሁልኑም ወይም አብዛኛውን ሕብረተሰብ ማዳረስ ሲቻል ነው።
Herd Effect የምንለው ደግሞ በ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ የ Herd Immunity በመኖሩ የ አንድ በሽታ ከ አንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ እድሉ ሲቀንስ ነው። ምን ያህሉ ሰው ለ አንድ በሽታ የመከላከል አቅም ሲኖረው ነው ይሄን Herd Effect የምናየው የሚለው የሚወሰነው በሽታው ምን ያህል ተላላፊ ነው በሚለው ነው።
---
Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
Further episodes of የጤና ወግ 🎙 Yetena Weg ®
Further podcasts by Yetenaweg@gmail.com
Website of Yetenaweg@gmail.com